Skip to content
Lyric
Dive
Public playlists
My playlists
Search
Sign in
Habte
Zéritu Kébédé
Popularity · Low
+
🇪🇹 Amharic · Original
0
0
Listen
YouTube
1
2
3
0:00 / 0:00
Loading YouTube player...
Lyrics offset
Synced
Lyrics
Original
Translation
Bilingual
የምወደው ነገር ሁሉ ተደራርቦ
በሱ ሊታይ ቻለ አንድ ላይ ተክቦ
ደስ የሚል ፀጋ ነው እሱን ማረግ የራስ
በእቅፉ ማሸለብ ደረቱን መንተራስ
ከናፍር ተዋደው በፍቅር ሲቀሉ
እንጆሪ ሲመስሉ ጣፋጭ የሚበሉ
እንዴት ያያስደስታል ከርሱ ጋር መጫወት
ሊመስለኝ አልቻለም ህልም እንጂ የእውነት
ሰው ባለው ይኮራል
እኔም በርሱ ሀብቴ
ያለኝ ጌጥ እርሱ ነው
መታያ ኩራቴ
አልማዝ እንቁ አይደለም
አይሸጥ አይለወጥ
ለእኔ ግን የት አለ
ከእርሱ የሚበልጥ
በፀጉሩ መሀከል ጣቶቼን ማንሸርሸር
በቀልድ በጨዋታ በፈገግታው መስከር
በፍቅር አፍዞኝ ዓይኑን ስመለከት
የፀደኩ መሰለኝ የገባሁኝ ገነት
በፍቅር ላይ ፍቅር እየጨማመረ
ሀብቴ ተትረፍርፎ በልቤ ላይ ከበረ
ይሄ ሁሉ ደስታ ይሄ ሁሉ ሀሴት
ሊመስለኝ አልቻለም ህልም እንጂ የእውነት
ሰው ባለው ይኮራል
እኔም በርሱ ሀብቴ
ያለኝ ጌጥ እርሱ ነው
መታያ ኩራቴ
አልማዝ እንቁ አይደለም
አይሸጥ አይለወጥ
ለእኔ ግን የት አለ
ከእርሱ የሚበልጥ
ፍቅር ይስጥሽ ብሎ ማን ነው የመረቀኝ
ይህን የመሰለ መልአክ የገጠመኝ
ሀብቴ መዋቢያዬ ጌጤ ብዬዋለው
ፍቅሬ ቅርስ ሆኖኛል እኔ ወደዋለው
ሰው ባለው ይኮራል
እኔም በርሱ ሀብቴ
ያለኝ ጌጥ እርሱ ነው
መታያ ኩራቴ
አልማዝ እንቁ አይደለም
አይሸጥ አይለወጥ
ለእኔ ግን የት አለ
ከእርሱ የሚበልጥ
ሰው ባለው ይኮራል
እኔም በርሱ ሀብቴ
ያለኝ ጌጥ እርሱ ነው
መታያ ኩራቴ
አልማዝ እንቁ አይደለም
አይሸጥ አይለወጥ
ለእኔ ግን የት አለ
ከእርሱ የሚበልጥ
ሰው ባለው ይኮራል
እኔም በርሱ ሀብቴ
ያለኝ ጌጥ እርሱ ነው
መታያ ኩራቴ
አልማዝ እንቁ አይደለም
አይሸጥ አይለወጥ
ለእኔ ግን የት አለ
ከእርሱ የሚበልጥ