Skip to content

Medina/Zelesegna

Popularity · Low

YouTube

Searching YouTube...

Lyrics

ወንድሜ ጠፍቶኝ ስሄድ ነብር አግኝቶኝ ከመንገድ አልተመለስኩም ወድያው ሄድኩ እኔን ይብላኝ እያልኩ አልተመለስኩም ወድያው ሄድኩ እኔን ይብላኝ እያልኩ የቀድሞ ዘመን ስህተት በፆም ቀን አሳ መብላት የአሁን ዘመን ሰው አያውቅ መላ በልቶም ሽሮ ነው ሚበላ የአሁን ዘመን ሰው አያውቅ መላ በልቶም ሽሮ ነው ሚበላ የኛ መድኃኒት አይነቶች በብዙ አሉ ቅመሞች ነገር ግን እኔ ሳስበው ስራስሩ መልካም ነው ነገር ግን እኔ ሳስበው ስራስሩ መልካም ነው ያባቶቻችን ውሃ ዋና ላይ ላዩን ነበር በጤና የዛሬ ልጆች ይበልጣሉ ወስጥ ለውስጥ ይሄዳሉ የዛሬ ልጆች ይበልጣሉ ወስጥ ለውስጥ ይሄዳሉ ኮሶ ተጣብቶኝ ትላንትና መድኃኒት ስሻን ዋልኩና ድንገት ሰማሁኝ አንድ ዜና የወዲያ ሰዎች ህግ ደንብ አይከለክልም ምግብ የኛስ ስርዓት ከባድ እንዲያው በባዶ ሆድ የኛስ ስርዓት ከባድ እንዲያው በባዶ ሆድ የጌታችንን ፀባይ ያለኔ የሚያውቅ አለ ወይ ማታ ለግብር መልካም ሰው ቀን ሲቆጣክ ክፉ ሰው ማታ ለግብር መልካም ሰው ቀን ሲቆጣክ ክፉ ሰው አያሳስትም ሰዓትን ቀጠሮ ያከብራል ሞት ሽማግሌ አይል ህፃን ሞት ጠያቂ ነው ሁሉን አሁን ይመጣል በእውነት ሞት ብሎ አይቀር ሞት አሁን ይመጣል በእውነት ሞት ብሎ አይቀር ሞት እሁድ ቅዳሜን ቢሆን እበላ ነበር ምሳዬን እንዲህ በጦም ቀን የምዞረው ለጊዜ ማድረሻ ነው እንዲህ በጦም ቀን የምዞረው ለጊዜ ማድረሻ ነው ትንሽ ቤት ሰራሁ እንደአቅመኛ ሁለት ሶስት ሰው የምታስተኛ አላስገባ አለች እሷው ጠባ ሰው በሰው ላይ እየገባ አላስገባ አለች እሷው ጠባ ሰው በሰው ላይ እየገባ ከታች ጉርጓዱ የጠለቀ ከላይ ጉበኑን የጠበቀ እንዲህም አርገው ሚሰሩት መፍረሱ አይቀርም ቤት እንዲህም አርገው ሚሰሩት መፍረሱ አይቀርም ቤት የዛሬ ዘመን ሰው ስራ ሳሩም ቅጠሉም አያኮራ እውቀቱስ ያንተ መሰለኝ በአብነት አድነኝ እውቀቱስ ያንተ መሰለኝ በአብነት አድነኝ አባቶቻችን ካህናት ሲጠመጥሙ ከጥንት ለስልጣናቸው ለክህነት መለያ ነበር ምልክት አሁንማ ጠምጣሞቹ ሹሞቹና ጠበቆቹ አሁንማ ጠምጣሞቹ ሹሞቹና ጠበቆቹ ይህች በቅሎዬ ምን ሆነች አጉል መጥፎ አመል ለመደች የጎረቤቷን እያየች ጭነት መገልበት አመጣች የጎረቤቷን እያየች ጭነት መገልበት አመጣች የሰሞኑ ጋብቻ ድንቅነቱ ከቀድሞ እጅጉን መለየቱ መሆኑ ቀርቶ እስከሞት ተጀመረ ተጧሪ ፈቶ እንታት ማግባት መሆኑ ቀርቶ እስከሞት ተጀመረ ተጧሪ ፈቶ እንታት ማግባት