Skip to content

Yeney Konjo

Popularity · Low

YouTube

Searching YouTube...

Lyrics

የኔ ቆንጆ የኔ ሸጋ ቁጭ በይ እናውጋ የኔ ቆንጆ የኔ ነሽ ወይ ልምጣ ልከተልሽ ወይ መቶ ሰው ቢሰለፍ አንቺን የማይመስለኝ ፍቅር ነው ህመም ነው በይ እስኪ ንገሪኝ አንቺን ባየሁበት ሌላ አልታይ ቢለኝ ጠረጠርኩት ልቤን ተነካሁ መሰለኝ ተነካሁ መሰለኝ በወር በ15 ቀን ከሆነ ነገሩ ሳላይሽ አልቀርም ይብዛ እንጂ ችግሩ ሰውነቴም ከሳ ልቤም ተጨነቀ ናፍቆቴም አልወጣ ፍቅሬም አላለቀ ፍቅሬም አላለቀ የኔ ቆንጆ የኔ ሸጋ ቁጭ በይ እናውጋ የኔ ቆንጆ የኔ ነሽ ወይ ልምጣ ልከተልሽ ወይ መንገዱ ቀጥታ የለውም ጎርበጥባጣ ደርሶ አደናቀፈኝ ያቺ ልጅ ብትመጣ ቀኑን አብረን ውለን አሁን ስንለያይ የቀረሽ መሰለኝ አይንሽን የማላይ አይንሽን የማላይ የኔ ቆንጆ የኔ ሸጋ ቁጭ በይ እናውጋ የኔ ቆንጆ የኔ ነሽ ወይ ልምጣ ልከተልሽ ወይ የኔ ቆንጆ የኔ ሸጋ ቁጭ በይ እናውጋ የኔ ቆንጆ የኔ ነሽ ወይ ልምጣ ልከተልሽ ወይ ሲጫወቱ ማማር ሲለብሱ መድመቅ ውብ እንደሷ ቆንጆ አይቼም አላቅ አንቺ አለሽኝ ብዬ ጠልቼ ሁሉንም እንደምን ከርታታ ብቸኛ ልሁን ብቸኛ ልሁን የኔ ቆንጆ የኔ ሸጋ ቁጭ በይ እናውጋ የኔ ቆንጆ የኔ ነሽ ወይ ልምጣ ልከተልሽ ወይ ከአጠገቤ ሆና ትጫወት ትሳቅ ከጥርሶቿ መሀል አለ የሚናፈቅ አልሰማ አልኩኝ እንጂ ልቤ የሚነግረኝን አሁን መች አጣሁት ለእኔ የሚሆነኝን ለእኔ የሚሆነኝን የኔ ቆንጆ የኔ ሸጋ ቁጭ በይ እናውጋ የኔ ቆንጆ የኔ ነሽ ወይ ልምጣ ልከተልሽ ወይ የኔ ቆንጆ የኔ ሸጋ ቁጭ በይ እናውጋ የኔ ቆንጆ የኔ ነሽ ወይ ልምጣ ልከተልሽ ወይ የኔ ቆንጆ የኔ ሸጋ ቁጭ በይ እናውጋ የኔ ቆንጆ የኔ ነሽ ወይ ልምጣ ልከተልሽ ወይ