Skip to content
Lyric
Dive
Public playlists
My playlists
Search
Sign in
Yene Alem
ብዙአየሁ ደምሴ
Popularity · Low
+
🇪🇹 Amharic · Original
0
0
YouTube
Searching YouTube...
Lyrics
Original
Translation
Bilingual
ሳዱላ ተሰርተሽ
አልቦሽን አርገሽ
ለሰው ሳትነግሪ ኮታ ደርበሽ
ዳገት ኮረብታውን ቤተስኪያኑን አልፈሽ
ነይ ነይ ገብል ሸጋ ጫካ ደኑን ጥሰሽ
የኔ አለም የት ነው የምትኖሪው
ንገሪኝ ልወቀው
የኔ አለም ያገር ልጅ ወገኔ
ቁጭ ብይ ከጎኔ
የኔ አለም አንቺ ካለሽበት
እራቀኝ ለመምጣት
ህልም ነሽ ቅዠቴ በሀሰት አልምልም
ለኔ አንቺ ነሽ እንጂ ሌላ አልተፈጠረም
ርቀቱ ነው ወይ አንቺ ያለሽበት
ቀኑ ረዘመብኝ የምትመጪበት
የኔ አለም ያሀገር ልጅ ወገኔ
ቁጭ ብይ ከጎኔ
የኔ አለም አንቺ ካለሽበት
ራቀኝ ለመምጣት
የኔ አለም የት ነው የምትኖሪው
ንገሪኝ ልወቀው
ሆዴ ተመግቦ የፍቅርሽን ድግስ
እረፍት አጣ ልቤ አንቺን በማስታወስ
ልቤ በመናፈቅ አንቺን እያሰበ
ላይሆን ጀምረነው ቀረ እንደተራበ
የኔ አለም ያሀገር ልጅ ወገኔ
ቁጭ ብይ ከጎኔ
የኔ አለም አንቺ ካለሽበት
ራቀኝ ለመምጣት
የኔ አለም የት ነው የምትኖሪው
ንገሪኝ ልወቀው
የኔ አለም አንቺ ካለሽበት
ራቀኝ ለመምጣት
የኔ አለም ያሀገር ልጅ ወገኔ
ቁጭ ብይ ከጎኔ
የኔ አለም የት ነው የምትኖሪው
ንገሪኝ ለወቀው