Skip to content
Lyric
Dive
Public playlists
My playlists
Search
Sign in
Yèné Felagoté
ጥላሁን ገሠሠ
Popularity · Low
+
🇪🇹 Amharic · Original
0
0
Listen
YouTube
1
2
3
0:00 / 0:00
Loading YouTube player...
Lyrics offset
Synced
Lyrics
Original
Translation
Bilingual
ሁሉም አውቆ እንዲኖሮ ሰብዐዊ መብቱን
ከፈጣሪ ፀጋ የተሰጠ ሀብቱን
ነበረ ምኞቴ ሰመረ መሰለኝ
ፍላጎቴ ደርሶ አይቸው ደስ አለኝ
እህህም... ብዬ
አለፍኩ ሁሉን ችዬ
አይ መከራዬ
ስል ሲፈስ እምባዬ
አልቀረም ግፉ
ሁሉም መታለፉ
ይህ ነው ምኞቴ
የኔ ፍላጎቴ
በከንቱ አልቀረም ጩኸቴ ተሰማ
ሁሉም ተረዳልኝ በፍቅር ተስማማ
የድካሜ ዋጋ የለፋሁበቱ
ይታሰብ ከእንግዲህ እንዳይቀር በከንቱ
እህህም... ብዬ
አለፍኩ ሁሉን ችዬ
አይ መከራዬ
ስል ሲፈስ እምባዬ
አልቀረም ግፉ
ሁሉም መታለፉ
ይህ ነው ምኞቴ
የኔ ፍላጎቴ
ከእንግዲህ ፍረዱኝ ጩኸቴን ስሙና
በእውነት ግልፅ ሚዛን ጊዜውን ለኩና
ብዙ ጊዜ አልፎኛል መከራዬን ሳዬ
የኔ ጩኸት ሆኖ ለሌሎች ሲሳይ
እህህም... ብዬ
አለፍኩ ሁሉን ችዬ
አይ መከራዬ
ስል ሲፈስ እምባዬ
አልቀረም ግፉ
ሁሉም መታለፉ
ይህ ነው ምኞቴ
የኔ ፍላጎቴ
ይህ ነው ምኞቴ
የኔ ፍላጎቴ
ይህ ነው ምኞቴ
የኔ ፍላጎቴ