Skip to content
Lyric
Dive
Public playlists
My playlists
Search
Sign in
Yefeker Wogagen
Bzunèsh Bèqèlè
Popularity · Low
+
🇪🇹 Amharic · Original
0
0
YouTube
Searching YouTube...
Lyrics
Original
Translation
Bilingual
በጭላንጭል የሚታየኝ ግሩም ድንቅ ሆኖ የፍቅር ዉጋጋ
መኖሬንም የሚያሳየኝ የሚያለመልም ነዉ ነፍስም ሆነ ስጋ
በጭላንጭል የሚታየኝ ግሩም ድንቅ ሆኖ የፍቅር ዉጋጋ
መኖሬንም የሚያሳየኝ የሚያለመልም ነዉ ነፍስም ሆነ ስጋ
የፍቅር ወጋጋን መኖሬን ገለጠዉ
ጭለማዉ ኑሮዬን በብርሃን ለወጠዉ
ጮራዉ ሲፈነጥቅ ከአለም ሁሉ ቀድሞ
በፍቅር ዉጋጋ ህይወቴ ለምልሞ
ልዙር ልንሸራሸር ቆላም ሆነ ደጋ ፥ ቆላም ሆነ ደጋ
በህይወቴ መብራት በፍቅር ዉጋጋ ፥ በፍቅር ዉጋጋ
በጭላንጭል የሚታየኝ ግሩም ድንቅ ሆኖ የፍቅር ዉጋጋ
መኖሬንም የሚያሳየኝ የሚያለመልም ነዉ ነፍስም ሆነ ስጋ
በጭላንጭል የሚታየኝ ግሩም ድንቅ ሆኖ የፍቅር ዉጋጋ
መኖሬንም የሚያሳየኝ የሚያለመልም ነዉ ነፍስም ሆነ ስጋ
እድል ሆነ ሀብትስ ምን ይቸግረኛል
መዉደድ መብራት ሆኖ ልቤን ገልጦልኛል
ምንኛ ጥሩ ነዉ ለወደዱት መሞት
የፍቅር ሀይል ነዉ ቁርጥ ያለ ሀሞት
ልዙር ልንሸራሸር ቆላም ሆነ ደጋ ፥ ቆላም ሆነ ደጋ
በህይወቴ መብራት በፍቅር ዉጋጋ ፥ በፍቅር ዉጋጋ
በህይወቴ መብራት በፍቅር ዉጋጋ ፥ በፍቅር ዉጋጋ