Skip to content

Site Engidih

Popularity · Low

YouTube

Searching YouTube...

Lyrics

ፍቅር ያጣ ይምጣ ፍቅር ያጣ ይምጣ ፌዝ መሳይ ጨዋታ ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ ፍቅር ያጣ ይምጣ ፍቅር ያጣ ይምጣ ፌዝ መሳይ ጨዋታ ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ ፍየል ወዲያ ሽመል ወዲህ በል እንዲያ በል እንዲህ ስጥ እንግዲህ በይ እንዲያ በይ እንዲህ ስጭ እንግዲህ ሰው የወሬ አምሮቱ ስር እየሰደደ ጮማ እየቆረጠ ሽንጥ እያወረደ ከጎድን ከሻኛው እያወራረደ ከዚህ ሁሉ ስጋ ምላስ ተወደደ ያራዳ ልጅ ሲባል እያለሳለሰ በአይኑ እየጠቀሰ በእጁ እየዳሰሰ መቼ ይሰስታል መስጠት ያውቅበታል የምታይው ህንፃ የእኛ ነው ይላታል ጉድ ጉድ ጉድ አልኩኝ ይሄን ካየሁ ወዲህ ስጥ እንግዲህ, መስጠት ስጥ እንግዲህ ስጥ እንግዲህ ሰው እንጀራን ንቆ ጭራሽ ላይኑ ጠልቶ መወፈር ጀመረ የጤፍ አሹቅ በልቶ በል እንዲያ በል እንዲህ ስጥ እንግዲህ በይ እንዲያ በይ እንዲህ ስጭ እንግዲህ ፍቅርን ስትለግስህ በምላሹ ስጣት ነፍስን አስደስተው እንደ ውሃ ሙላት በል እንዲያ በል እንዲህ ስጥ እንግዲህ በይ እንዲያ በይ እንዲህ ስጭ እንግዲህ ፍቅር ያጣ ይምጣ ፍቅር ያጣ ይምጣ ፌዝ መሳይ ጨዋታ ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ ፍቅር ያጣ ይምጣ ፍቅር ያጣ ይምጣ ፌዝ መሳይ ጨዋታ ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ ፍየል ወዲያ ሽመል ወዲህ በል እንዲያ በል እንዲህ ስጥ እንግዲህ በይ እንዲያ በይ እንዲህ ስጭ እንግዲህ ላም ከሰማይ ወርዳ ወተቷ ታለበ ሰው በህልም እንጀራ በተስፋ ጠገበ ሰው በሬን ጠላና በዶሮ ታረሰ ማኛው ነጭ ጤፉ በቁና ታፈሰ ያራዳ ልጅ ሲሰጥ ልብ እየዋለለ በአይኑ እየታለለ በአፉ እየደለለ አይቶ ያጠምድና ቀርቦ ያለምድና ልቧን ይረከባል ትንሽ ይሰጥና ጉድ ጉድ ጉድ አልኩኝ ይሄን ካየሁ ወዲህ ስጥ እንግዲህ, መስጠት ነው ስጥ እንግዲህ ስጥ እንግዲህ ስልቻ ቀለቀሎ, ቀልቀሎ ስልቻ ዝም ብለሽ ተቀበይ የሰጡሽን ብቻ በል እንዲያ በል እንዲህ ስጥ እንግዲህ በይ እንዲያ በይ እንዲህ ስጭ እንግዲህ እየተሰጣጡ ካልሆነ ዘመኑ አይነቃነቅም አይገፋም ቀኑ በል እንዲያ በል እንዲህ ስጥ እንግዲህ በይ እንዲያ በይ እንዲህ ስጭ እንግዲህ ለሰጪ እግዜር ይስጠው ካለው ላይ ጨምሮ ተቀባዩ ሁሉ ሰጪ ነው ዘንድሮ በል እንዲያ በል እንዲህ ስጥ እንግዲህ በይ እንዲያ በይ እንዲህ ስጭ እንግዲህ ፍቅርን ስትለግስህ በምላሹ ስጣት ነፍስን አስደስተው እንደ ውሃ ሙላት በል እንዲያ በል እንዲህ ስጥ እንግዲህ በይ እንዲያ በይ እንዲህ ስጭ እንግዲህ በል እንዲያ በል እንዲህ ስጥ እንግዲህ በይ እንዲያ በይ እንዲህ ስጭ እንግዲህ በል እንዲያ በል እንዲህ ስጥ እንግዲህ በይ እንዲያ በይ እንዲህ ስጭ እንግዲህ በል እንዲያ በል እንዲህ ስጥ እንግዲህ በይ እንዲያ በይ እንዲህ ስጭ እንግዲህ