Skip to content
Lyric
Dive
Public playlists
My playlists
Search
Sign in
Betarikih
ሀና ተክሌ
Popularity · Low
+
🇪🇹 Amharic · Original
0
0
YouTube
Searching YouTube...
Lyrics
Original
Translation
Bilingual
ክቡር የሰው ልጅ ክቡር በሰማይ በምድር
የአንድ ዘር ቅጂ የአንድ ነፍስ ስፍር
አሻራ መልኩ ቢለይ ቀለሙ
ወርቁ ሲፈተሽ አንድ ነው ደሙ
ከጎሳ ከዘር ከባህል ትውፊት
ከሀገርም በላይ ከብሄር በፊት
አብ የፈጠረው በሁሉ አንግሶ
ወልድ የሞተለት ደሙን አፍስሶ
ሰው ነው ክቡር ሰው የተከበረ
በአምላክ እግዚአብሔር የተመተረ
ምኑን ቢለያይ ድንበር አብዝቶ
አንድ አድርጎታል ክርስቶስ ሞቶ
ክቡር ክቡር ክቡር
ክቡር ክቡር ክቡር
ክቡር ክቡር ፍጡር
ክቡር ክቡር ክቡር
በታሪክ ማይገናኘውን
የታሪክ ልዩነት ያለውን
የዘር የዳር ድንበር ያበጀውን
በምንም በምንም ጭራሽ ማይገጥመውን
ኢየሱስ በታሪክህ አንድ አደረግከው
በታሪክ አገናኘኸው
በመስቀልህ አንድ አደረግከው
በመስቀልህ አገናኘኸው
ጨዋ የለም
ባሪያ የለም
ጉራማይሌውን አንድ አደረግህ
ማይገናኘውን አገናኘህ
ህዝብ ልጅ አንተ አባት ተባልህ
ህዝብ ልጅ አንተ አብ አባት ተባልህ
ጉራማይሌውን አንድ አደረግህ
ማይገናኘውን አገናኘህ
ህዝብ ልጅ አንተ አባት ተባልህ
ህዝብ ልጅ አንተ አብ አባት ተባልህ