Bati
Popularity · Low
YouTube
Searching YouTube...
Lyrics
ትናንትና ማታ፤ በደጅሽ አልፌ
ልቤን ትቼ መጣሁ፤ ሳንባዬን ታቅፌ
ምነው ባደረገኝ፤ የደጅሽን አፈር
አንቺ ስትረግጪኝ እኔ እንድንፈራፈር
እኔ እንድንፈራፈር
ሄደች አሉ ከቤቴ በላይ
አይኗን ሳላይ
ከጥንት ነው፤ ከመሠረቱ
ፍን ፍን ይወዳል ቤቱ
ከመልእክተኛዉም አለው ገደቢስ
የለችም ይለኛል ከደጇ ሳይደርስ
ከደጇ ሳይደርስ
በስማም በስማም ሰይጣኑን ፈርቼ
ብዙ የለመድኩት ብቻዬን ቀርቼ
ብቻዬን ቀርቼ
አወይኔ ወይኔ ወይኔ ዘንድሮ
ካንቺ መለየቴ ሆነብኝ እሮሮ
ሆነብኝ እሮሮ ሆነብኝ እሮሮ
እኔ ራሴን አሞኝ ተኝቼ ባልጋ ላይ
ወዴት ትሄጂያለሽ ሞት ሽረቴን ሳታይ
ታመሽ ታምሜያለሁ፤ ሲያክሙሽም ደም ወጣኝ
ስትሞች ግን አልሞትም ድሃው ምን በወጣኝ
ደሃው ምን በወጣኝ
ሄደች አሉ ከቤቴ በላይ አይኗን ሳላይ
ሄደች አሉ ጋራ ጋራውን ነፋሻውን
ትናንትና ማታ፤ በደጅሽ አልፌ
ልቤን ትቼ መጣሁ፤ ሳንባዬን ታቅፌ
ምነው ባደረገኝ፤ የደጅሽን አፈር
አንቺ ስትረግጪኝ እኔ እንድንፈራፈር
እኔ እንድንፈራፈር
ሄደች አሉ ከቤቴ በላይ
አይኗን ሳላይ
ከጥንት ነው፤ ከመሠረቱ
ፍን ፍን ይወዳል ቤቱ
ከመልእክተኛዉም አለው ገደቢስ
የለችም ይለኛል ከደጇ ሳይደርስ
ከደጇ ሳይደርስ፤ ከደጇ ሳይደርስ
እኔ ራሴን አሞኝ ተኝቼ ባልጋ ላይ
ወዴት ትሄጃለሽ፤ ሞት ሽረቴን ሳታይ
ሞት ሽረቴን ሳታይ
ታመሽ ታምሜያለሁ ሲያክሙሽም ደም ወጣኝ
ስትሞች ግን አልሞትም ደሃው ምን በወጣኝ
ደሃው ምን በወጣነኝ ሁሁሁ ደሃው ምን በወጣኝ
ኦሆሆ ኦሆሆሆሆሆ
ኦሆሆ ሆሆሆ
ሆሆሆ...
(አለቀ።)