Skip to content
Lyric
Dive
Public playlists
My playlists
Search
Sign in
Abay Weyes Vegas
ጎሳዬ ተስፋዬ
Popularity · Low
+
🇪🇹 Amharic · Original
0
0
YouTube
Searching YouTube...
Lyrics
Original
Translation
Bilingual
ሠመረ አሉኝ ህልምሽ
መንገድ ስትመኚ
መሄድሽ ነው አሉኝ
ብቻ ደና ሁኚ
ኢትዮጵያዬ እማማዬ
ላንቺ የተባለ ገና አዲስ ቀን አለ
እኔስ ሃገር አለኝ ሁሌም አይሞላ
ሰው ሃገር ሄጄ ነፍሴን አልጠላ
መናዬ የት ነሽ በሚልሽ ልቤ
ሄድኩኝ ብቻዬን ሃሳብ ደርቤ
አንቺ ቬጋስ ልሂድ ብለሽ የኔን ጉዳይ ለማን ጥለሽ
እኔ ሃገሬን ስል ዓባይ መፅናኛዬን እሱን ሳይ
አንቺም ወደሽ አይደለም, ሆ
ቢገድሽ እንጂ ስደት, ሆ
ልብሽስ ከኔ ጋር ነው, ሆ
አውቃለሁኝ የውነት, ሆ
ሰው ችግር ቢያስጨንቀው, ሆ
ከሀገሩ ተሰደደ, ሆ
ሆድ ይፍጀው ብሎ ሄዶ, ሆ
አይለምዱትን ለመደ, ሆ
በሰው ሃገር ላይ ሆኖ, ሆ
ወርቅ እንኳን ቢታፈስ, ሆ
ደርሶ የህሊና እዳ ነው, ሆ
ትልቅ ሆኖ ማነስ, ሆ
ሆ ሆ ሆ ሆ ሆ ሆ ሆ ሆ
እኔስ ሃገር አለኝ ሁሌም አይሞላ
ሰው ሃገር ሄጄ ነፍሴን አልጠላ
መናዬ የት ነሽ በሚልሽ ልቤ
ሄድኩኝ ብቻዬን ሃሳብ ደርቤ
አንቺ ቬጋስ ልሂድ ብለሽ የኔን ጉዳይ ለማን ጥለሽ
እኔ ሃገሬን ስል ዓባይ መፅናኛዬን እሱን ሳይ
እንደ ቆቅ በቋፍ ኑሮ, ሆ
ሰው ምድሩን መናፈቁ, ሆ
ታከተኝ የሚሉበት, ሆ
መቅረቡ አይቀርም የሩቁ, ሆ
እንኳንስ በአፈርሽ ላይ, ሆ
የተቀበረ እትብቱ, ሆ
የሰው ዘር ማህፀን ነው, ሆ
የፍጡር ሁሉ እናቱ, ሆ
የናቁሽ ፊት የነሱሽ, ሆ
ከእግርሽ ላይ ይወድቃሉ, ሆ
ማዕበሉን ሰንጥቆ, ሆ
ቀን ሲፈርድ ይመጣሉ, ሆ
አንቺም ወደሽ አይደለም, ሆ
ቢገድሽ እንጂ ስደት, ሆ
ልብሽስ ከኔ ጋር ነው, ሆ
አውቃለሁኝ የውነት, ሆ
ሰው ችግር ቢያስጨንቀው, ሆ
ከሀገሩ ተሰደደ, ሆ
ሆድ ይፍጀው ብሎ ሄዶ, ሆ
አይለምዱትን ለመደ, ሆ
በሰው ሃገር ላይ ሆኖ, ሆ
ወርቅ እንኳን ቢታፈስ, ሆ
ደርሶ የህሊና እዳ ነው, ሆ
ትልቅ ሆኖ ማነስ, ሆ
ኢትዮጵያዬ, ሆ እማማዬ, ሆ
ላንቺ የተባለ, ሆ ገና አዲስ ቀን አለ, ሆ
ሆ ሆ ሆ ሆ ሆ ሆ ሆ ሆ ሆ ሆ ሆ ሆ