Skip to content

Sèw Nèw Yètchèkènè

Tilahun Gèssèssè
Popularity · Low

Listen

YouTube

0:00 / 0:00
Loading YouTube player...
Lyrics offset
Synced

Lyrics

"እወቁ እንዳትደክሙ በሀሳብ ዘመቻ ፍቅር ያጋራ ነው አይደለም የብቻ" (፪) ሲዋደዱ እኮ ነው እራስ መውደድ ቀርቶ የፍቅር ውጤቱ የሚታየው ጎልቶ ፍቅር ካልተያዘ እመሀል ቤት ሆኖ አንዱን ያስደስታል አንዱን አሳዝኖ "እወቁ እንዳትደክሙ በሀሳብ ዘመቻ ፍቅር ያጋራ ነው አይደለም የብቻ" (፪) ፍቅርም ጨከነ ምነው ማለታችሁ የማይጠፋ ደስታ ሲሰጥ እያያችሁ የፍቅርን ስሜት ቀምሶ የተረዳ ምንም አይሰማው በብዙም ቢጎዳ "እወቁ እንዳትደክሙ በሀሳብ ዘመቻ ፍቅር ያጋራ ነው አይደለም የብቻ" (፪) ክፋት የለበትም ፍቅር እንደሆነ ያመኻኛል እንጂ ሰው ነው የጨከነ ባ'ለም ላይ አይተናል የሚበቃ ሰጪ ፍቅር እኮ አይደለም ጨካኝ ሰው ነው እንጂ "እወቁ እንዳትደክሙ በሀሳብ ዘመቻ ፍቅር ያጋራ ነው አይደለም የብቻ" (፪) ፍቅር ያጋራ ነው አይደለም የብቻ አይደለም የብቻ አይደለም የብቻ