Skip to content
Lyric
Dive
Public playlists
My playlists
Search
Sign in
Merkato Sefere
Abdu Kiar
Popularity · Moderate
+
Original
0
0
Listen
YouTube
1
2
3
0:00 / 0:00
Loading YouTube player...
Lyrics offset
Synced
Lyrics
Original
Translation
Bilingual
አንቺ አዲስ አበባ ማየቱን ተውሽ ወይ
አሳድገሽ ሲጠፋ የታሉ አትይም ወይ
ጨዋ ደግ ልጆችሽ ውበትሽ ናፍቋቸው
ተሰቃዩ ብዙ እባክሽ ጥርያቸው
እንኳን ላሳደግሽው ጥሬሽን ለበላ
ለስንቱ ጎረቤት ሆነሻል ከለላ
እናታችን ሀገር ፍቅርሽ ለብቻ ነው
ደጅሽን ብንረግጥ ኑ ብትይን ምንድነው
መቼም የገባው ቀን ከሀገር ከመንደሬ
ደስታ ነው እሚሰማኝ ገና ሳየው መርካቶ ሰፈሬ
ችላ ችላ አትበይ አይተሽ መቸገሬን
ሌላ እናት የለኝም ከአንቺ ሌላ ውቢቷ ሀገሬ
የወግ የልማዱን ሊያደርጉ ሲጥሩ
በያሉበት ሀገር ሀበሾች ሲጣራ
ሲሰበሰቡማ ሲደምቅ ጨዋታቸው
አንቺ ነሽ አው ሸገር ትልቁ አርስታቸው
ጤፍ እንኳን ባይገኝ በማሽላ እንጀራ
የአገር ቀሚስ ለብሳ እህታችን ብትኮራ
በነጭ በአረብ ሀገር ቢሆንም ኑሯቸው
ኢትዮጵያን ማየት ነው ትልቁ ህልማቸው
መቼም የገባው ቀን ከሀገር ከመንደሬ
ደስታ ነው እሚሰማኝ ገና ሳየው መርካቶ ሰፈሬ
ችላ ችላ አትበይ አይተሽ መቸገሬን
ሌላ እናት የለኝም ከአንቺ ሌላ ውቢቷ ሀገሬ
Nobody can fix this up
Nobody can bring peace up
Africans are always out
While dem love dem green land
Who's gonna be blamed for this
When at last war, not peace
Ethiopians in somebody's land
Calling as the refugees
The love I've got for A.A
And for the people who is living there
I can't wait until I see my hood
Until I breeze natural air
Only Lord can lemme live
Peacefully in a Zion of Land
My wish in paradise in Addis Ababa town
መቼም የገባው ቀን ከሀገር ከመንደሬ
ደስታ ነው እሚሰማኝ ገና ሳየው መርካቶ ሰፈሬ
ችላ ችላ አትበይ አይተሽ መቸገሬን
ሌላ እናት የለኝም ከአንቺ ሌላ ውቢቷ ሀገሬ