Skip to content
Lyric
Dive
Public playlists
My playlists
Search
Sign in
Endet Lechalew
ብዙአየሁ ደምሴ
Popularity · Low
+
🇪🇹 Amharic · Original
0
0
Listen
YouTube
1
2
3
0:00 / 0:00
Loading YouTube player...
Lyrics offset
Synced
Lyrics
Original
Translation
Bilingual
ሰው ሁሉ ሰምቶት መውደዴን
ሀገር አውቆልኝ ማፍቀሬን
የልቤን ሁሉ ነግርያት
እንዴት ልቻለው ስለያት
ሰው ሁሉ ሰምቶት መውደዴን
ሀገር አውቆልኝ ማፍቀሬን
የልቤን ሁሉ ነግርያት
እንዴት ልቻለው ስለያት
የእውነተኛ ፍቅር መድረሻው ክልሉ
መድረሻው ክልሉ
ካ'ጠገብ ሲገኝ ነው መውደድ ከነ አካሉ
መውደድ ከነ አካሉ
ናፍቆት የሚሰማው ጧት ማታ እያደረ
ጧት ማታ እያደረ
ለወደደ ሰው ነው ካ'ንጀት ላፈቀረ
ካ'ንጀት ላፈቀረ
ባ'ንቺ እንደማልጨኽን ልቤ እየገመተኝ
ልቤ እየገመተኝ
ካንቺ መለየቱ ካንቺ መለየቱ ካንቺ መለየቱን
መወሰን አቃተኝ
የመውደድ ገመናን ካልቻሉ መሸፈን
ካልቻሉ መሸፈን
ይህ አይደለም እንዴ ይህ አይደለም እንዴ
ይህ አይደለም እንዴ ሳይሞቱ መከፈን
ሰው ሁሉ ሰምቶት መውደዴን
ሀገር አውቆልኝ ማፍቀሬን
የልቤን ሁሉ ነግርያት
እንዴት ልቻለው ስለያት
ባ'ጥር በግድግዳ ስሟ ይነበባል
ስሟ ይነበባል
እሷ ስትጠራ ልቤ ይበተናል
ልቤ ይበተናል
ጓዝሽ ተጠቅልሎ ሄደሽ ተሰናብተሽ
ሄደሽ ተሰናብተሽ
ምን ቀረሽ ከሆዴ አላለቅሽም ወጥተሽ
አላለቅሽም ወጥተሽ
ተሰናብተሽኛል አንቺን ሸኝቻለሁ
አንቺን ሸኝቻለሁ
የልቤን እንግዳ የልቤን እንግዳ የልቤን እንግዳ
ፍቅርሽን ይዣለሁ
ፍቅርሽ እያየለ ጨኽኖ እየጣለኝ
ጨኽኖ እየጣለኝ
ልቤን ማን ይውቀሰው ልቤን ማን ይውቀሰው
ልቤን ማን ይውቀሰው አንቺን አንቺን ሲለኝ
ሰው ሁሉ ሰምቶት መውደዴን
ሀገር አውቆልኝ ማፍቀሬን
የልቤን ሁሉ ነግርያት
እንዴት ልቻለው ስለያት
ሰው ሁሉ ሰምቶት መውደዴን
ሀገር አውቆልኝ ማፍቀሬን
የልቤን ሁሉ ነግርያት
እንዴት ልቻለው ስለያት
እኔማ ምን አለኝ ሳላያት አላድር
ሳላያት አላድር
አስቀምጫታለሁ ካለሁበት ምድር
ካለሁበት ምድር
ፈራሁት ፍቅርሽን ወዶ መተዉን
ወዶ መተዉን
የሰው ፍቅር ይዞ መሸሽ መራቁን
መሸሽ መራቁን
ቢሰጡኝማ ልብ የተደላደለ
የተደላደለ
እቆርጥ አልነበር ወይ በጅምሩ ሳለ
በጅምሩ ሳለ
ሳይፈልጉት መጥቶ ቢሹት አይገኝም
ሲሹት አይገኝም
ልቤን ባላሳየው ፍቅር አይደፍረኝም
ፍቅር አይደፍረኝም
ሜዳ ያህል ከብዶኝ እንዴት ልዋል ልደር
እንዴት ልዋል ልደር
ምነው ባላየሁሽ ምነው ባለየሁሽ ምነው ባላየሁሽ
ባልገባሁ ሰው መንደር
ይባስ ብሎ ጣለኝ ፍቅር ከማላውቀው
ፍቅር ከማላውቀው
እርም የለኝም እኔ እርም የለኝም እኔ
እርም የለኝም እኔ አልማር ካለፈው
እርም የለኝም እኔ እርም የለኝም እኔ
እርም የለኝም እኔ አልማር ካለፈው